Welcome to Addis Ababa City Food and Drug Administration and Authority Kirkos Branch Cluster 1 Office!       እንኳን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድኃኒትና ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ሳይንስን መሠረት ያደረገ የምግብ፣ መድሃኒት፣ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ስራ ተዘርግቶ ነዋሪዎቿ የቁጥጥሩ ባለቤት የሆኑበትና ጤናማ ማህበረሰብ የሚኖርባት ከተማ ሆና ለማየት ይተጋል!

የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን
ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ጽ/ቤት

የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን
ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ጽ/ቤት

የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን
ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ጽ/ቤት

የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን
ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ጽ/ቤት

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

በጤናው ዘርፍ ሰፍኖ የቆየውን የተበታተነና ጥራት የጎደለውን የአስተዳደርና የቁጥጥር ስርአት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ አዲስና የተቀናጀ የምግብ፤የመድሀኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 391/1995 አንቀፅ 14/1/ሀ እና የፌደራል መንግስት የምግብ፤መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 661/2002 አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የምግብ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 30/2004 እስከ ወረዳ ድረስ ተቋቁሞ በአዋጁ በተሠጠዉ ስልጣን መሰረት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የጀመረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 ምግብና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ የከተማዋን ነዋሪዎች ጤንነት ለመጠበቅ ፣የምግብ እና የጤና ነክ ምርቶች ጥራት፣ደህንነት እና ውጤታማነት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን የማረጋገጥ ስራ...... ተጨማሪ ያንብቡ

ሲ/ር ሳራ ዮሀንስ , የቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 የምግብና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

በጽ/ቤቱ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

በቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 የምግብና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ ጽ/ቤት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች:-

Photograph

የጽ/ቤቱ ቡድን መሪና ባለሙያዎች

የቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 የምግብና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድኃኒትና ባለስልጣን የቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 1 የምግብና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡